የግሪን ፓርቲን ዕጩ ይገናኙ፡ አድሪያና ሙኛቶ-ሃሙ

Adriana’s Amharic flyer text:

አድሪያና ሙኛቶ-ሃሙ ለብሔራዊ ምርጫ የግሪን ፓርቲ ዕጩ ተወዳዳሪ ናቸው።  ስለ አየር ጠባይ ለውጥና የተፈጥሮ ሃብት መራቆት የሚጨነቁና ለካናዳ ልጆች የተሻለ ዕድል መገንባት የሚሹ ሰው ናቸው።

ግሪን ፓርቲ የተፈጥሮ ምንጮችን በመጠቀም ብዙ ትውልዶችን ሊያደላድል የሚችል ምጣኔ ሃብትን በመገንባት ላይ ያተኩራል።  የልጅ ልጆቻችን እንዲከፍሉባቸው ሳናስገድድ የመንግሥት አገልግሎቶችን በሚዛናዊነት ማዳረስ እንሻለን።

አድሪያያና ሙኛቶ-ሃሙ ቶሮንቶ-ዳንፎርዝን በመወከልና ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ንጹህና ጤናማ ማህበረሰብ እንዲመሠረት ይረዳሉ።  ለርስዎ ጠቃሚው ምን እንደሆን ማወቅ ይፈልጋሉ።  በሥ.ቁ 416-800-5020 ለአድሪያና በአማርኛ መልዕክት ይተው።  ወይም ለአድሪያና በአማርኛ በኢሜል አድራሻቸው adriana@danforthgreens.ca ይጻፉላቸው፤ ይመልስሎታል።

አድሪያናን እደግፋለሁ፤ ምክንያቱም ለካናዳ ግሪን ፓርቲ ዕጩ ተመራጭነቱዋ ለተፈጥሮ እንክብካቤ፣ ለማህበራዊ ፍትህ፣ ለአሳታፊ ዴሞክራሲ፣ ለሰላምና ለተለያዩ ባህሎች መከበር ስለምትቆም።
— ሙሉቀን ሙጨ (Muluken Muchie)

የካናዳ ግሪን ፓርቲ መመሪያዎች በስድስት መርሆዎች ላይ የተመሠረቱ ናቸው፤ …

Leave a comment

To weed out spam, your comment will not appear right away.